አጠቃላይ እይታ

መድሃኒት ማዕከል ፋርማሲ በቶሮንቶ፣ በኪችነር፣ በወተርሉ፣ በካምብሪጅ፣ በጉወልፍ፣ በለንደን እንዲሁም በጂትኤ(GTA) እና አቅራቢያዋ የሚያገለግል በአማርኛ እና በትግርኛ ቋንቋ ጭምር ግልጋሎትን የሚሰጥ ፋርማሲ ነው። የፋማሲያችን ባለሞያ ከሃያ አመት በላይ የስራ ልምድ ያላቸው ሲሆኑ እናንተን ለማንኛውም አይነት የፋርማሲ አግልግሎት ለማስተናገድ ተዘጋጅተው ይጠብቋችኋችል።

በሽታን ለመከላከልም ሆነ ጤናዎን ለመጠበቅ ከፈለጉ ወደ ፋርማሲያችን ዛሬውኑ ይደውሉ። ከቤት መውጣት ባይችሉ ምንም አያስቡ እቤትዎ ድረስ አገልግሎት እንሰጣለን። ዛሬውኑ ካሉበት ሆነው በመደወል የፋርማሲ ባለሞያዎችን ያናግሩ። ደግሞም ወደ አገር ቤት የህመም ማስታገሻና ሌሎችም ማዘዣ ለማያስፈልጋቸው መድሃኒቶች እና ቫይታሚኖች መላክ ቢያስፈልጎት ይደውሉልን። ትክክለኛ የሆነ ምክርን ያለምንም ክፍያ እንሰጣለን።

ይደውሉልን የመድሃኒት ማዘዣ ፋይሎችዎን ካሉበት ፋርማሲ ወደ እኛ ያለምንም ክፍያ እናስተላልፋለን።

የእኛ ተልዕኮ

የበሽተኞች የጤና እንክብካቤ ፍላጎቶቻቸውን እንዲለዩ እና በትክክል እንዲያገኙ እንረዳቸዋለን

በመድሃኒት ማዕከል ፋርማሲ ውስጥ አንድ ለአንድ የሆነ ያለምንም ክፍያ የምክር አገልግሎት እና የመድሃኒት አወሳሰድ ስልጠና እንሰጣለን። አገልግሎታችን በጥራት እና በተቀላጠፈ መልኩ ማቅረብ ተልዕኳችን ነው።

አዛውንቶች የሚገባቸውን እክብካቤ ለመስጠት በባለሙያ የታገዘ ለመድሃኒት አቅርቦት መፍትሄዎችን እንሰጣለን። የማሕበረሰብ ጤናን እና ደህንነት ለማጎልበት ቆርጠን ተነስተናል!

የእኛ እሴቶች

በመድሃኒት ማእከል ፋርማሲ፣ ርህራሄን፣ ታማኝነትን እና የላቀ ደረጃ ያለው አገልግሎት እንሰጣለን። ግላዊ እንክብካቤን ለመስጠት፣ ከፍተኛ የአገልግሎት ጥራት ደረጃዎችን ለመጠበቅ እና በማህበረሰባችን ውስጥ እምነትን ለመገንባት ቁርጠኞች ነን። የእርስዎን ደህንነት ለመጠበቅ እኛ የምንሰራው ሁሉም ነገር በማስተዋል እና ትክክለኛ መረጃ በመጠቀም ብቻ ነው።

ለታማሚዎች ቅድሚያ

ለእርሶ ፍላጎት ቅድሚያ እንሰጣለን

ለጤናዎ ትጋት

ለጤንነትዎ በትጋት እንሰራለን

ታማኝነት

ትክክለኛ መረጃን በታማኝነት እንሰጣለን

ምርጥነት

ልዮና ድንቅ የሆነ አገልግሎት እንሰጣለን

ፋርማሲስት ያግኙ

እሌኒ በልሁ

ፋርማሲስት እና ስራ አስኪያጅ
BSc (Hons), PharmD, R.Ph.

የግል ምክር ያለ ክፍያ ያግኙ!

ፋርማሲስቶቻችን የእርስዎን ጤና እና ደህንነት ለማሻሻል ከፍተኛ ዝግጅት አድርገው ይጠብቁዎታል።