ምን ቀን እና ምን ሰዓት ላይ ነው ፋርማሲያችሁ ክፍት የሆነው?
ፋርማሲያችን ሰኞ, ማክሰኞ, ረቡዕ, ሐሙስ, አርብ፣ ቅዳሜ እና እሑድ ከጠዋቱ 9 am እስከ 5 pm ድረስ ለአገልግሎት ክፍት ነው። ደውለው ያናግሩን!
የመድሃኒት ማዘዣዎች ከሌላ ፋርማሲ ወደ እናተ ማስተላለፍ እችላለሁ?
አዎን ይችላሉ! ከእርሶ የምንፈልገውን ማዘዢያ ይለበትን ፋርማሲ እንዲያነጋግሩን ብቻ ነው። እኛ ዝውውሩን ያለምንም ክፍያ እና ምንም ሳናዘገይ በቶሎ እናስተላልፋለን።
ልዩ ግልጋሎቶችን ትሰጣላችሁን?
አዎ እንሰጣለን! ፋርማሲያችን የተለያዩ ልዮ ግልጋሎቶችን ይሰጣል። ለስኳር በሽታ ምክር፣ የደም ግፊት ወይም የኦክስጂን መጠን መለካት ስልጠና። አስምን የመቆጣጠር እና የአስም መተነፈሻ አጠቃቀም ስልጠና፣ ሲጋራ ለማቆም የሚረዱ እገዛዎች እንዲሁ የተለያዩ ግልጋሎቶችን እሰጣለን። ለበለጠ መረጃ ያገግልግሎት ድህረ ገጻችንን ይመልከቱ።
ምን ዓይነት ምርቶች በፋርማሲያችሁ ታቀርባላችሁ?
በሐኪም ማዘዢያ እና የሐኪም ማዘዢያ የማያስፈልጋቸውን መድሐኒቶ፣ ቫይታሚኖች እና የተለያዩ ጤናን የሚያሻሽሉ መጽሐኒቶችን እና ማገዢያዎችን እንይዛለን። ለበለጠ መረጃ ይደውሉ እና ይጠይቁን።
ሜድ ቼክ (MedsCheck) ምን ማለት ነው?
ሜድ ቼክ የመድሃኒት ግምገማ እና የጤና ምክክር አገልግሎት በ(OHIP) የሚሸፈን ከእርሶ ምንም ክፍያን የማይጠይቅ የመድሃኒት ግምገማ እና የጤና ምክክር አገልግሎት ነው። መድሃኒቶን በትክክል መውሰድዎን ወይም ሌላ ጥያቄዎቾን ለመመለስ ሞያው ያላቸው ፋርማሲስት መድሃኒቶችዎን ከእርስዎ ጋር ይገመግማሉ። ይህም ጤናዎን በሚገባ መልኩ መጠበቅ እንዲችሉ የመድሃኒት አጠቃቀሞን ለማገዝ ነው። ዛሬውኑ ደውለው ይህን አገልግሎት ያለክፍያ ይጠቀሙ።
ያለቁ መድሃኒቶቼን እንዴት ማስሞላት እችላለሁ?
በመደወል በስልክ ያስሞሉ (866) 791-1311 ነገር ግን ቀኑን ጠብቀን እኛ እንድናስተውሶት ወይም ያሉበት ቦታ ድረስ በቀኑ እንድናደርስሎት ከፈለጉ ስልኮትን እኛ ጋር ደውለው ያስመዝግቡ። ያለምንም ክፍያ በቀኑ ተከታትለን እናስታውሶታለን።
ምን አይነት ኢንሹራንስ ትቀበላላችሁ?
ሁሉንም አይነት ተአማኒነት ያላቸውን ኢንሹራሶች እንቀበላለን። የበለጠ መረጃ ስለ ኢንሹራንሶ የሚሸፍነውን ክፍያ ለማወቅም ሆነ ኢንሹራንሱ ተቀባይነት እንዳለው ለማረጋገጥ ደውለው ይጠይቁን እንነግሮታለን። ከኢንሹራንስም የሚያስፈልጎትን መረጃ ቀድመው ማዘጋጀት እንዲችሉ ምክር እንሰጣለን።
የመላክ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ?
አዎን! ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 9am እስከ ምሽቱ 8pm ሰዓት ድረስ ከሶስት በላይ መድሃኒት የሚወስዱ ከሆነ መድሃኒት አቅርቦትን ያለምንም ክፍያ ያሉበት ድረስ እናደርሳለን።
እንዴት ፋርማሲስት ማናገር እችላለሁ?
ለፈጣን መልስ በዚህ ስልክ ደውሉ (866) 791-1311 ድንገት በስራ ተጠምደን ስልክ ካላነሳንሎት መልዕክት ይተውልን ወዲያውኑ መልሰን እንደውላለን። በአማርኛ ሆነ በትግርኛ ማናገር ከፈለጉም ምንም ችግር የለውም በሁለቱም ቋንቋ እናገለግላለን።
የመድኃኒት ግምገማዎችን ይሰጣሉ?
አዎ እንሰጣለን! ምንም አይነት የመድሃኒቶች በጋጨት በጤናዎ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ስለሚወስዷቸው መድሃኒቶች በባለሞያ የታገዘ ግምገማ እንሰጣለን።
የመድሃኒት ውሕድ ቅመማ አገልግሎት ትሰጣላችሁ?
አዎ እንሰጣለን! አንዳንድ መድሃኒቶች ለሕመምተኛው በልዩ ትእዛዝ ለታማሚው ጤና በሚመች ሁኔታ በፋርማሲስት መድሃኒቱን እንዲያስቀምም ይታዘዛል። የእኛም ፋርማሲ በሞያተኞቻችን ይህንን የመድሃኒት ውሕድ ቅመማ በተቀላጠፈ መልኩ አዘጋጅተን ለታማሚው እንሰጣለን። ዛሬውኑ ይደውሉ!
ሲጋራ ለማቆም ፈልጌ ነበር እገዛ ትሰጣላችሁ?
አዎ እንሰጣን! ሲጋራ ሱሶን ለመቆጣጠር ወይም ለማቆም የሚያግዙ ምክሮችን፣ ስልጠናዎችን እና ለመቆጣጠር የሚያግዙ ግብዓቶች እናቀርናለን። ዛሬውን ደውለው ያለምንም ክፍያ ምክር ያግኙ። ጤናዎ በእጅዎ ነው!
መድሃኒት ለመቆጣጠር የሚያችሉ ስልጠናዎች ትሰጣላችሁ?
አዎን እንሰጣለን! የተለያዩ መድሃኒቶችን መቆጣጠር እንዲችሉ እና አጠቃቀማቸውን እንዲያውቁ ያለ ምንም ክፍያ ስልጠና እንሰጣለን።
በአስም ለሚሰቃዩ አገልግሎት ትሰጣላችሁ?
አዎ እንሰጣለን! አስማችሁን እንዴት መቆጣጠር እንድምትችሁ፣ የመድሃኒት ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ አጠቃቀሞች ዙርያ ያለምንም ክፍያ ስልጠና እንሰጣለን። አሁኑ እርዳታ ለማግኘት ይደውሉልን።
ፋርማሲስቶች ለበሽተኛ ምክር ለመስጠት ዝግጁ ናቸው?
አዎን ዝግጁ ናቸው። የእኛ ፋርማሲስቶች ስለ መድሃኒቶችዎ ለመወያየት፣ ለጥያቄዎችዎ መልስ ለመስጠት እና ለግሎ የተበጀ የጤና ምክር ለመስጠት እንዲሁም ለአንድ ለአንድ ምክክር ዝግጁ ናቸው። ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ሞልተው ይላኩ ወይም በቀጥታ ይደውሉልን።.
ያለ ክፍያ የግል ምክር ያግኙ.
በኢ-ሚይል እኛ ለማግኘት
የስራ ሰዓቶቻችን
- ሰኞ: 9am — 5pm
- ማክሰኞ: 9am — 5pm
- ሮብዕ :1 pm — 5pm
- ሐሙስ:9am — 5pm
- አርብ: 9am — 5pm
- ቅዳሜ: 9am — 5pm
- እሁድ: 9am — 5pm