መደበኛ

  • በሃኪም ማዘዢና ያለማዘዢያ
    የታዘዙትን መድሃኒት ለመግዛት፣ ለመሙላት ወይም ያለ ማዘዢያ መውሰድ የሚችሉት መጽሃኒት ለማግኘት ዛሪውኑ ይደውሉ።

  • ቫይታሚኖችን ጤና ደጋፊ ኪኒኖች
    የተለያዩ ቪይታሚኖችን እንይዛለን፣ የተፈጥሮ ግብዓት ያለባቸው ቫይታሚኖችንም እንይዛለን ዛሪውኑ ይደውሉ።

  • የተፈጥሮ ምርቶች
    ምንም ጎጂ ኬሚካል ያልተካተተባቸው የተፈጥሮ ውጤት የሆኑ ቫይታሚን እና ምርት ለማግኘት ዛሪውኑ ይደውሉ።

  • የቁስል ልብሶች
    ጉዳቶችን ለማከም የተለያዩ የቁስል እንክብካቤ አቅርቦቶችን እንዲሁም ለተለያዩ አይነት ቁስሎች መሸፈኛዎች አሉን ዛሪውኑ ይደውሉ።

  • ጥብቅ አድርገው የሚይዙ ካሊሲዎች
    የደም ዝውውርን ለማሻሻል እና የተለያዩ የእግር እብጠቶችን ለመከላከል የሚስችሉ ካልሲዎች አሉ። ከፈለጉም በልኮም እናዘጋጃለን።
  • የቤት ውስጥ የጤና እንክብካቤ ምርቶች
    በቤት ውስጥ ጤናን እና የግል እንክብካቤን ለመቆጣጠር አስፈላጊ ምርቶችን በፋርማሲያችን ያገኛሉ። ዛሪውኑ ይደውሉ።

ልዮ

  • የስኳር በሽታ ምክር እና ስኳር መከታተል
    የስኳር በሽታ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን በብቃት ስለመጠቀም የባለሙያዎች መመሪያ እና ስልጠና ያላክፍያ እንሰጣለን።

  • አስም በሽታን መቆጣጠር
    ስለ አስም አያያዝ እና ትክክለኛ የአተነፋፈስ መሳሪያ አጠቃቀም ስልጠና እና ያለምንም ክፍያ የባለሙያ ምክር እንሰጣለን።
  • የመድሃኒት ማደራጃ የላስቲክ ሳጥን
    የመድሃኒት መውሰጃ ቀን እና ሰዓት ለማቃለል ያለክፍያ የመድሃኒት ማደራጂያ ላስቲክ ሳጥን እኛ ጋር ለሚሰለጥኑ ሁሉ እነሰጣለን።

  • የመድሃኒት ውሕድ ቅመማ
    ለእርሶ ሰውነት ብቻ የሚሆን በትዕዛዝ ብቻ ተቀምሞ የሚዘጋጅ መድሃኒትን በፋርማሲያችን እንቀምማለን።

  • ሲጋራ ሱስ ለማቆም ያለክፍያ ስልጠና
    የኒኮቲን ሱስን ለማሸነፍ እና ጤናዎን ለማሻሻል እንዲረዳዎ ግላዊ ዕቅዶችን እና ምክር አገልግሎት ያለክፍያ እንሰጣለን። እንዲሁም ለማቆም በሚረዱ መድሃኒቶች ዙሪያ ምክር እንሰጣለን።

  • በልክ የሚሰሩ ካልሲዎች
    የደም ዝውውርን የሚረዱ ካልሲዎችን በራሶ ልክ በመመተር በልኮ እናዘጋጃለን።

  • ሜድ ቼክ (MedsCheck)
    የመድሃኒት ግምገማ እና የጤና ምክክር አገልግሎት በኦህፕ OHIP የሚሸፈን ከእርሶ ምንም ክፍያን የማይጠይቅ የመድሃኒት ግምገማ እና የጤና ምክክር አገልግሎት ነው። ዛሬውኑ በመደወል የዚህ አገልግሎ ተጠቃሚ ይሁኑ።

ለአዛውንቶች

  • ወዳጃዊ የሆነ የግል ድጋፍ እንሰጣለን
    ጠቅላላ ጤናዎን ለመጠበቅ እንዲችሉ የሚፈልጉትን እገዛ ለእርሶ ተስማሚ በሚሆን መልኩ እንደ ወዳጆ ሆነን ድጋፍ እንሰጣለን።

  • የፋርማሲስት ምክር
    በስራው ብዙ አመት ልምድ ባካበቱ ሙያተኛ ፋርማሲስቶቻችን አንድ ለአንድ በግሎ ምክርን ያለምንም ክፍያ ዛሬውኑ ደውለው ይቀበሉ።

  • ያለክፍያ የብሊስተር ጥቅል አገልግሎቶች
    ለቀላል የመድሃኒት አስተዳደር የብሊስተር ማሸጊያዎችን ከእኛ ያለምንም ክፍያ ያግኙ።

  • በርዎ ድረስ መድሃኒት ያለክፍያ ማድረስ
    ከሥስት በላይ መድሃኒቶች የሚወስዱ ከሆነ ያለ ምንም ወጪ መድሃኒትዎን እቤትዎ ድረስ አናቅርበናል። ደውለው ይጠይቁን!

  • የስልክ ክትትል
    በስልክ እየደወልን ስለ መድሃኒቶ ክትትል እንድናደርግሎት ይፈልጋሉ? ይደውሉ እና ስልኮን እኛ ፋርማሲ ያስመዝግቡ ደውለን እናማክሮታለን። ተገቢውንም ክትትል በመረጡት ሰዓት ደውለን እናደርግሎታለን።

  • መድሃኒት ግምገማ ያለክፍያ
    የህክምና እቅድዎን ለማመቻቸት ያለ ምንም ክፍያ የመድሃኒት ግምገማ ከፋርማሲስት ጋር ሆነው መድሃኒቶን ያስገምግሙ።

አንድ ለአንድ ምክር ከእኛ ያለ ምንም ክፍያ ማግኘት ይፈልጋሉ?

በሽታን ለመክላከል እና ጤና ለመጠብቅ ምክር ይፈልጋሉ? ከታች ያለውን መስፈንጠሪያ በመጫን ወደ ቅጽ መሙያው በመሄድ ጥያቄዎን ይላኩልን። ፋርማሲስስት ለጥያቄዎ መልስ ይሰጥዎታል።

የግል ምክር ያለ ክፍያ ያግኙ!

ፋርማሲስቶቻችን የእርስዎን ጤና እና ደህንነት ለማሻሻል ከፍተኛ ዝግጅት አድርገው ይጠብቁዎታል።